← Back to Education

Education

How Category "B" Business Tax is Calculated under Ethiopia's Updated Law (Proclamation No. 1395/2025)

የደረጃ "ለ" ግብር ከፋይ ማን ነው? በአዲሱ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 50 መሠረት፣ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች በደረጃ "ለ" ይፈረጃሉ፡

By Ephrem Gebeyehu
    • የሽያጭ/ገቢ መጠን፡ በግብር ዓመቱ ውስጥ ጠቅላላ ዓመታዊ የሽያጭ/የገቢ መጠናቸው ከብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በታች የሆነ ማንኛውም ግለሰብ ነጋዴ።

    ከአሰራሩ የተገለሉ አካላት፡ የሙያ አገልግሎት ሰጪዎች (የሕግ፣ የሂሳብ፣ የምክር፣ የሕክምና አገልግሎት ሰጪዎች) VAT ተመዝጋቢዎች፣ የሕግ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች (/የተ/የግ/ማ፣ .) እና ሙሉ የሂሳብ መዝገብ በመያዝ በትርፍ ላይ ግብር ለመክፈል የመረጡ ነጋዴዎች በጠቅላላ የሽያጭ ግብር ስሌት አይስተናገዱም። እነዚህ አካላት የደረጃ "" የሂሳብ መዝገብ መያዝ አለባቸው።

    የደረጃ "" ጠቅላላ የሽያጭ/ገቢ ግብር አሰላሰል ደንብ (አንቀጽ 50)

    ሙሉ የሂሳብ መዝገብ ለማይይዙ የደረጃ "" ግብር ከፋዮች ግብር የሚሰላው ከድርጅቱ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ/ሽያጭ (Gross Receipts) ላይ በቀጥታ በመቶኛ ተሰልፎ ነው፡

    የጠቅላላ ሽያጭ ገቢ ግብር ተመኖች፡

    ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ መጠን (በብር)

    የግብር ተመን (%)

    0 – 100,000

    2%

    100,001 – 500,000

    3%

    500,001 – 1,000,000

    5%

    1,000,001 – 1,500,000

    7%

    1,500,001 – 2,000,000

    9%

    የግብር አሰላሰል ምሳሌ

    ምሳሌ፡ በሽመላ ወይም ችርቻሮ ንግድ የተሰማሩ ግለሰብ በበጀት ዓመቱ ያገኙት ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ 1,200,000 ብር ቢሆን፡

    • የግብር ተመን፡ 1,200,000 ብር 1,000,001 – 1,500,000 ብር እርከን ውስጥ ስለሚወድቅ የሚመለከተው የታክስ ተመን 7% ነው።
    • ስሌት፡ .
    • ጠቅላላ የሚከፈለው የንግድ ትርፍ ግብር፡ 84,000 ብር